#የሀሳብ_ዕቁብ_እንጣል ✍️ ብዙ ሰው ገንዘቡን ቆጥቦ ሕይወቱን ወደፊት ለማራመድ ሲል ከገቢው ቀንሶ፣ ከፍጆታው ቀምቶ እቁብ ይጥላል፡፡ ጥሩ ነው እቁብ መጣል፡፡ ብዙ ሰው ግን በገንዘቡ ዕቁብ አንደሚጥለው ሁሉ ማንነቱን ለማብሰል፣ ምንነቱን ለመረዳት፣ የሕይወት መንገዱን ለማደላደል፣ በራሱ ላይ ድልን ለመጎናፀፍ፣ የተሻለ ማንነት ያለው ሰው ለመሆን ሲል የሃሳብ ዕቁብ ሲጥል አይታይም፡፡ ✍️ ሃሳብ እንደገንዘብ የችግር ጊዜ ደራሽ ነው፡፡ አብዛኛው ሰው ችግሩን ለመፍታት የሚሞክረው በገንዘቡ ብቻ ነው፡፡ ገንዘብ ኖሮ ችግርን የሚቋቋም ጠንካራ ሃሳብ ከሌለ ዋጋ የለውም፡፡ የበሰለ ሃሳብ ኖሮ ገንዘቡ ባይኖር ብዙም ችግሩ አይባባስም፡፡ ሃሳቡ ችግርን መሻገሪያ ገንዘብን መፍጠር ይችላልና፡፡ የበሠለ ሃሳብ ከጨለማ ሕይወት የሚያወጣ ድልድይ ነው፡፡ አሻጋሪና ተሻጋሪ ሃሳብ መፍጠር የሚቻለው ቀድመን በጣልነው የሃሳብ ዕቁብ ነው፡፡ የተከማቸ ሃሳብ ዕውቀትን ይገነባልና፡፡ ✍️ ሰው ጤናማ ስሜት፣ የተረጋጋ ሕይወት፣ የበሠለ ማንነት፣ የሃሳብ ልዕልና እንዲኖረው ከዚህ በላይ ሃብት፣ ከዚህ በላይ የትምህርት ደረጃ፣ ከዚህ በላይ የስልጣን ሹመት፣ እንደዚህ ዓይነት ወዳጅና ቤተሰብ ሲኖረው ነው የሚል የተሠመረ ወይም የተቀመጠ መስመርም ሆነ ድምዳሜ የለም፡፡ ይሄን ሁሉ እውን እንዲሆን የሚያደርገው የሰው የገዛ ራሱ ሃሳብ ነው፡፡ ሃሳቡ ዕውቀት ሆኖ በተግባር ሲፈተን በየትኛውም ጊዜ ለሚደርስበት የኑሮ ውጣውረድ ችግሩን መፍቻ ቁልፍ ሆኖ ያገለግለዋል፡፡ ምክንያቱም ጤናማ ያልሆኑ ስሜቶችና የሕይወት ውሳኔዎች ጤናማ ካልሆነ ሃሳብና አመለካከት የሚመነጩ ናቸው፡፡ ✍️ ጤናማ አስተሳሰብን መፍጠር የሚቻለው ደግሞ ሰው ከሃሳቦቹ ጋር መጨዋወት፣ መሟገት፣ አልፎ ተርፎም ...
Welcome to Yeshaneh Tube. Join our website and gate right information at the right time Yeshaneh Tube Path of wisdom