በኢትዮጵያ እስከ 3ኛ ክፍል ያሉ 56 በመቶ የሚሆኑ ተማሪዎች ምንም ዓይነት ቃላት ማንበብ እንደማይችሉ ተነገረ‼️
የሀገር አቀፍ ፈተናዎች ኤጀንሲ "ኢትዮጵያ ታንብብ" በሚል ባዘጋቸው ጉባኤ ላይ ያከናወነውን ጥናት ይፍ አድርጓል። ጥናቱም በተለያዩ ክልሎች የሚገኙ 401 ትምህርት ቤቶች ላይ የተደረገ መሆኑን የተገለፀ ሲሆን በጥናቱ የትግራይ ክልል አለመካተቱ ተነግሯል።
የዚህ ጥናት ተሳታፊ የሆኑት የሀገር አቀፍ ፈተናዎች ኤጀንሲ የትምርት ምዘናና ምርምር መሪ ስራ አስፈፃሚ ዳይሬክተር ዶክተር ኢፍ ጉርሙ እንደተናገሩት 56 በመቶ የሚሆኑ የ2ኛ እና የ3ኘ ክፍል ተማሪዎች አንድም ቃላት ማንበብ እንዳልቻሉ ገልፀዋል።
ይህ ቁጥር ከባለፉት አመታት ጋር ሲነፃፀር በመጠኑ መሻሻል አሳይታል የተባለ ሲሆን ከሁለት አመት በፊት የተደረገው ጥናት ምንም ማንበብ የማይችሉት 63 በመቶዎች እንደነበሩ ጠቁመዋል።
ለዚህም እንደምክንያት የተቀመጡት መምህራን ከአምስቱ የትምህርት ቀናት አራቱን መምህራን ይፅፋሉ ተማሪዎች ይገለብጣሉ ምንም የማንበቢያ እድል አይሰጣቸውም ሲሉ ዶክተር ኢፍ ጨምረው ተናግረዋል።
በሌላ በኩል 70 በመቶ መምህራን አዲሱን የስረዓተ ትምህርት ስልጠና አለመውሰዳቸው እና 75 በመቶ መፀሀፍ ለተማሪዎች አለመድረሱ ለችግሩ መባባስ እንደምክንያት ተቀምጧል።
ኢትዮጵያ ንባብ በ1998 በዩናይትድ ስቴትስ ኦፍ አሜሪካ የተመሰረተ እና በ2002 ዓ.ም በኢትዮጵያ የተመዘገበ መንግሥታዊ ያልሆነ ድርጅት ሲሆን
የህጻናትን የማንበብ ባህል ለማሳደግ እና ለማዳበር በመላው ኢትዮጵያ በሚገኙ ክልሎች እየሰራ የሚገኝ ድርጅት ነው።
ድርጅቱ ከሩብ ሚሊዮን በላይ መጽሃፍቶችን በመላክ እና ከ130,000 በላይ ህጻናትን በዓመት እያገለገለ ሲሆን ከ70 በላይ ቤተ-መጻሕፍት ማቋቋሙን አስታውቋል።
Comments
Post a Comment