Skip to main content

Posts

Showing posts from April 13, 2025

Grade 12 Biology Unit 3: Part 5 (#1): Cellular respiration ‪

“ ተማሪዎች ወደ ትምህርት ቤት ስልክ ይዘው እንዳይሄዱ ለማድረግ እንቅስቃሴ ተጀምሯል “ - ብርሃኑ ነጋ (ፕሮፌሰር)

ተማሪዎች ወደ ትምህርት ቤት ስልክ የሚባል ነገር ይዘው እንዳይገቡ ለማድረግ እንቅስቃሴ መጀመሩን ትምህርት ሚኒስቴር አሳወቀ። የትምህርት ሚኒስትር ብርሃኑ ነጋ (ፕሮፌሰር) በሚመሩት የትምህርት ዘርፍ ላይ ስለአፈጻጻምና ስለታቀዱ እቅዶች ማብራሪያ ሰጥተዋል። በሰጡት ማብራሪያም በሚቀጥለው ሳምንት ከትምህርት ቢሮዎች ጋር ውይይት እንደሚካሄድ ጠቁመዋል። በዚህም ወቅት ተማሪዎች ስልክ ትምህርት ቤት ይዘው እንዳይገቡ ለማድረግ ስለሚደረገው እንቅስቃሴ እንደሚመከር ገልጸዋል። “ የጋራ ስምምነት ላይ ከደረስን ከሚቀጥለው ዓመት ጀምሮ ተማሪዎች ትምህርት ቤት ገብተው ትምህርት መከታተል ነው እንጂ ከስልክ ጋር የሚጫወቱበት ሁኔታ እንዳይፈጠር ይደረጋል “ ብለዋል። 

ተማሪ ያላሳለፉ 700 ት/ቤቶች

በ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ምንም ተማሪ ያላሳለፉ 700 ትምህርት ቤቶችን ለማብቃት እቅድ ተይዞ እየተሰራ መሆኑን የትምህርት ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡ የትምህርት ሚኒስቴር ሰራተኞች በዘጠኝ ወራት እቅድ አፈጻጸም ላይ ውይይት አድርገዋል። የትምህርት ሚኒስትር ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር) በዚህ ወቅት እንደገለጹት÷ የመንግስት ትምህርት ቤቶችን በማብቃት ጥራት ያለው ትምህርት ለዜጎች ሁሉ ለማዳረስ እየተሰራ ነው። በሁሉም መስክ ያለውን ችግር መፍታት የሚቻለው መሃንዲሶች፣ ቴክኖሎጂስቶች፣ ቴክኒሻኖችና ሌሎችን ባለሙያዎች በጥራትና በብቃት ማፍራት ሲቻል ነው ብለዋል፡፡ የት/ቤቶችን ደረጃ በማሻሻል፣ መምህራንን አቅም በማሳደግና በሌሎች የአጠቃላይና ከፍተኛ ትምህርት ዘርፎች የተጀመሩ የሪፎርም ሥራዎች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ ተናግረዋል፡፡ በ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ምንም ተማሪ ያላሳለፉ 700 ት/ቤቶችን ለማብቃት እቅድ ተይዞ እየተሰራ ነው ማለታቸውንም የሚኒስቴሩ መረጃ ያመላክታል፡፡ በመድረኩ የተገኙት የኢንዱስትሪ ሚኒስትር መላኩ አለበል በበኩላቸው÷ በትምህርት ላይ የሚደረግ ኢንቨስትመንት እጅግ ትልቁ ተግባር መሆኑን ጠቁመው፤ ከዚህ አንጻር እየተሰራ ያለው ስራ ተስፋ ሰጭ መሆኑን ተናግረዋል።  ትምህርት ላይ እየተደረገ ያለው ሪፎርም ሌሎችንም ተቋማት ሊቀይር የሚችል መሆኑን ነው የገለጹት የገለጹት፡፡ በተፈጥሮና በሰው ሰራሽ ችግር ከትምህርት ገበታ ውጪ የሆኑ ተማሪዎች ወደ ትምህርት ቤት እንዲመለሱ የሚደረገው ጥረት ተጠናክሮ ሊቀጥል እንደሚገባም አጽንኦት ሰጥተዋል፡፡ @yeshanehtube

ጸጸትን የሚያስከትሉ ነገሮች

በወጣትነት ጊዜያችን ስለ ወደፊቱ ብዙም ሳናስብ የተለያዩ ውሳኔዎችን እናደርጋለን። አንዳንድ ጊዜ እነዚህ ውሳኔዎች በመካከለኛ ዕድሜያችን ላይ ክፉኛ ዋጋ ያስከፍሉናል። አንድ ሰው ሲያረጅ ሊጸጸትባቸው ከሚችላቸው ነገሮች መካከል ጥቂቶቹ እነዚህ ናቸው፦ 1. ያልተጠቀምንባቸው አጋጣሚዎች በወጣትነታችሁ ብዙ በሮች ይከፈታሉ፣ ብዙ እድሎች ታገኛላችሁ። ብዙ ወጣቶች በፍርሃት፣ በስንፍና ወይም በትዕቢት ምክንያት እነዚህን አጋጣሚዎች ያልፏቸዋል። ነገር ግን ወጣትነትና ጉልበት እያለ አዲስ ሥራ ለመጀመርና ለራሳችሁ ስም ለመገንባት ምርጡ ጊዜ ነው። አንዳንዶች እድሎቹ ለእነርሱ በጣም ትልቅ እንደሆኑ ያስባሉ። እነዚህን አጋጣሚዎች ተጠቀሙባቸው፤ አለበለዚያ አንድ ቀን ስታረጁ ወደ ኋላ ተመልሳችሁ እነዚያን ያመለጡ እድሎች ለመያዝ ትመኛላችሁ። 2. ያፈረስናቸው ድልድዮች (ያቋረጥናቸው ግንኙነቶች) በወጣትነት ጊዜያችን ለግንኙነቶች ብዙም አንጨነቅም፤ አብዛኛው ሰው የሚያስበው በማንኛውም ዋጋ ገንዘብ ማግኘትና የስኬት መሰላልን መውጣት ነው። ብዙዎች ለመሻሻል ሲሉ ሰዎችን ይጠቀማሉ ይረግጣሉም፤ ግንኙነቶችን እንደ ቀላል ነገር ይቆጥራሉ፣ ትስስሮችን ያበላሻሉ፣ ለግል ጥቅማቸው ሲሉ ከሰዎች ጋር ይተኛሉ። ነገር ግን እነዚህ መጥፎ ድርጊቶች ወደፊት ዋጋ ያስከፍሏችኋል። ህይወት ያለ ፍቅርና ጓደኞች ምን ያህል ባዶ እንደሆነ ስትገነዘቡ። ስኬታማ ስትሆኑ ነገር ግን በዙሪያችሁ ማንም ሳይኖር ወይም የሚታመን ሰው ስታጡ። 3. ያበላሸነው ሰውነት በሙሉ ህይወታችሁ የምትኖሩበት አንድ ሰውነት ብቻ ነው ያላችሁ። የምታጨሱት ሲጋራ፣ አብዝታችሁ የምትጠጡት አልኮል፣ የምትወስዱት አደንዛዥ ዕፅ፣ የምትመገቡት ጤናማ ያልሆነ ምግብ፤ ይህ ሁሉ ቀስ በቀስ ያጠፋችኋል። በ50 ዓመታችሁ የአኗኗር ዘይቤ በሽታዎች ሲይዟችሁ፣ በ...