Skip to main content

Posts

Showing posts from October 27, 2024

Grade 12 Biology Multiple question with answer

Prepared by: Yeshaneh Adimasu  Yeshaneh Tube Instruction: Choose the correct answer from the given alternatives  1. ________ is a mission-oriented science that focus on the protection and restoration of biodiversity and the diversity of life on the earth.   A/ Environmental Biology                    C/ Conservation Biology B/ Developmental biology                    D/ Systematic Biology   Answewr: C 2. Which one of the following is not the importance of protecting natural resources? A/ Protect wildlife and preserve it for future generations B/ Improve water quality and air quality C/ Preserve open and green spaces D/ Increase exploitation of natural resources by humans Answewr: D  3 . ________ is a strategy of increasing the micronutrients level in food group through...

የ93 አመት እድሜ ባለጸጋ አዛውንት መልዕክት

 የ93 አመት እድሜ ባለጸጋ አዛውንት በድንገት ራሳቸውን ይስቱና መተንፈስ አቅቷቸው ወደ ሆስፒታል ይወስዳሉ። እናም ለ 24 ሰዓታት ኦክስጅን ተሰጥቷቸው ይቆያሉ። ከጥቂት ሰዓት በኋላ ተሽሏቸው ወደቤታቸው እንዲመለሱ ተወሰነ።  ዶክተሩም ‘’እስካሁን ለተደረገልዎት የህክምና እርዳታ 5000 ዶላር መክፈል ይጠበቅብዎታል’’ ይልና ሂሳቡን ያሳያቸዋል።  አዛውንቱም ሂሳቡን አይተው ማልቀስ ጀመሩ።  ዶክተሩ በሂሳቡ ምክንያት ከሆነ እንዳያለቅሱ ነገራቸው። አዛውንቱ ግን "በገንዘብ ምክንያት አላለቅስም።  ገንዘቡን በሙሉ መክፈል እችላለሁ።  ያለቀስኩበት ምክንያት ለ 24 ሰአታት ኦክሲጅን በመጠቀሜ 5000 ዶላር መክፈል አለብህ አላችሁኝ።  ነገር ግን 93 አመት ሙሉ ፈጣሪዬ የሰጠኝን አየር ስተነፍስ ቆይቻለሁ።  ግን ይህን ያህል ዘመን ምንም አልከፍልም ነበር። ከፈጣሪዬ ምን ያህል ዕዳ እንዳለብኝ ታውቃለህ? ይህ ቸርነቱ ነው ያስለቀሰኝ።’’ ብለው መለሱለት። ዶክተሩም አንገቱን ደፍቶ ስቅስቅ ብሎ ማልቀስ ጀመረ። ይህን ለምታነቡ ሁሉ፣ ለፈጣሪ ምንም የምንከፍለው ነገር ሳይኖር ለዓመታት ነፃ አየር ስንተነፍስ ኖረናል፣ እንኖራለንም።   በህይወታችን ውስጥ ይህን ሁሉ በገንዘብ የማይተመን አገልግሎት በነፃ ለሰጠን ፈጣሪያችን 2 ሰከንድ ብቻ ወስደን ማመስገን ይከብደናል?

አፍሪካ የ15 ሚሊየን መምህራን እጥረት አጋጥሟታል

በአኅጉሪቱ የ15 ሚሊየን መምህራን እጥረት ማጋጠሙን የአፍሪካ ኅብረት አስታውቋል፡፡ የአፍሪካ ኅብረት የትምህርት፣ የሣይንስ፣ ቴክኖሎጂ እና ኢኖቬሽን ኮሚሽነር መሐመድ ባልሆሲን በሰጡት መግለጫ፥ የመምህራን እጥረቱ በአኅጉሪቱ  አሉታዊ ተጽዕኖ እያሳደረ መሆኑን አስገንዝበዋል፡፡ በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት (ተመድ) የተቀመጠውን በትምህርት የ2030 የዘላቂ ልማት ግቦችን ለማሳካት አኅጉሪቱ የተፈጠረውን ክፍተት ለማስተካከል ርምጃ እንድትወስድ ጠይቀዋል። የመምህራን እጥረቱን ለመሙላትና በትምህርት ሥርዓቱ ላይ ኢንቨስት የሚደረገውን በአግባቡ ለመጠቀምም ጠንካራ ጥረቶች እንደሚያስፈልጉ አስረድተዋል፡፡ በአፍሪካ የመምህራን እጥረትን ለመፍታት፣ የትምህርት መሠረተ ልማቶችን ለማሻሻል፣ የዘላቂ ልማት ግቦችን በተያዘላቸው ጊዜ ለማጠናቀቅ 90 ቢሊየን የአሜሪካ ዶላር እንደሚያስፈልግም አስታውቀዋል፡፡ በአፍሪካ ያለው የትምህርት ሥርዓት የተሻለ ውጤት እንዲያስመዘግብ ዓለም አቀፍ ድጋፍ እንዲደረግ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

በጀርመን የወፏ ቤት እንዳይፈርስ ተደረገ

በጀርመኗ ቲዩቢንገን ከተማ በሚገኝ የዩኒቨርሲቲ ክሊንክ ጣሪያ ላይ አንዲት ወፍ ጎጆዋን ቀልሳ መኖር ከጀመረች ከራርማለች። ይህች ወፍ እንደሌሎች ዝርያቸው በመጥፋት አደጋ ላይ ከሚገኙ የወፍ ዓይነቶች አንዷ ናት። የዩኒቨርሲቲ ክሊኒኩ የሕንጻ ማስፋፋት ሥራ ለማከናወን በተሰናዳበት አጋጣሚ በጣሪያው ጎጆዋን ቀልሳ የምትኖረውን ወፍ ይደርሱባታል። ክሊኒኩም በማስፋፋት ፕሮጀክቱ መቀጠሉን ይገታል። 250 ሚሊየን ዩሮ የሚያወጣው ፕሮጀክትም ለዘጠኝ ዓመታት ባለበት ቆመ። በአካባቢው የሚገኘው ደን ጥበቃውም ቀጠለ፤ ወፏም ያለ ስጋት በጣሪያው ላይ ትኖር ጀመር። የወፎን ሁኔታ በቅርብ የሚከታተሉ ባለሙያዎች ታዲያ ድንገት ወፏ ትሰወርባቸዋለች። ዘሯ ሊጠፋ ነው የተባለላት ወፍ አለመኖር ግን ወዲያው የታቀደውን የሕንጻ ማስፋፋት ፕሮጀክት መጀመር አላስቻለም። በጥንቃቄና በትዕግሥት ወፏ ወደ ቀለሰችው ጎጆዋ ትመለስ ይሆናል በሚል ተጠበቀች። ጉዳዩ የግዛቷ ፖለቲከኞችና ምክር ቤት መነጋገሪያ ሆነ። ድመት በልቷት ይሁን ወይም አካባቢውን ለቃ ባልታወቀ ምክንያት የወፏ ከጎርጎሪዮሳዊው 2022 ጀምሮ አለመታየት በደስታ የማስፋፋት ሥራውን ለመጀመር አላጣደፈም። ይልቁንም የለመደችው አካባቢ ነውና ተመልሳ ብትመጣ ጎጆዋ ከፈረሰ የት ትገባለች የሚል ክርክር አስነሳ። የከተማዋ ከንቲባ ወፏ አሁን እኛ ሳናባርራት ቦታውን ስለለቀች ሥራው መቀጠል ይችላል ቢሉም የጀርመን የተፈጥሮ ጥበቃ ሕግ ባለሙያዎች ግን አንቀጽ እየጠቀሱ ሞገቱ። የአእዋፍ ጥናት ባለሙያዎችም በዚህ እየተሳተፉ ነው። ይህች ወፍ ፈጣሪ አድሏት ጀርመን ሀገር በመኖሯ ጎጆዋ ሳይፈርስ የዩኒቨርሲቲ ክሊኒኩን የማስፋፊያ ፕሮጀክት አጓተተ። ግንባታውን ለማድረግ በአካባቢው ከሚገኘው ደን የተወሰነው ይወገዳል መባሉም ሌላ ሙግት አስነስቷል።

Grade 11 Biology Unit 2 (Part 3): Reproduction in Animals