Skip to main content

በጀርመን የወፏ ቤት እንዳይፈርስ ተደረገ



በጀርመኗ ቲዩቢንገን ከተማ በሚገኝ የዩኒቨርሲቲ ክሊንክ ጣሪያ ላይ አንዲት ወፍ ጎጆዋን ቀልሳ መኖር ከጀመረች ከራርማለች። ይህች ወፍ እንደሌሎች ዝርያቸው በመጥፋት አደጋ ላይ ከሚገኙ የወፍ ዓይነቶች አንዷ ናት። የዩኒቨርሲቲ ክሊኒኩ የሕንጻ ማስፋፋት ሥራ ለማከናወን በተሰናዳበት አጋጣሚ በጣሪያው ጎጆዋን ቀልሳ የምትኖረውን ወፍ ይደርሱባታል። ክሊኒኩም በማስፋፋት ፕሮጀክቱ መቀጠሉን ይገታል። 250 ሚሊየን ዩሮ የሚያወጣው ፕሮጀክትም ለዘጠኝ ዓመታት ባለበት ቆመ። በአካባቢው የሚገኘው ደን ጥበቃውም ቀጠለ፤ ወፏም ያለ ስጋት በጣሪያው ላይ ትኖር ጀመር። የወፎን ሁኔታ በቅርብ የሚከታተሉ ባለሙያዎች ታዲያ ድንገት ወፏ ትሰወርባቸዋለች።

ዘሯ ሊጠፋ ነው የተባለላት ወፍ አለመኖር ግን ወዲያው የታቀደውን የሕንጻ ማስፋፋት ፕሮጀክት መጀመር አላስቻለም። በጥንቃቄና በትዕግሥት ወፏ ወደ ቀለሰችው ጎጆዋ ትመለስ ይሆናል በሚል ተጠበቀች። ጉዳዩ የግዛቷ ፖለቲከኞችና ምክር ቤት መነጋገሪያ ሆነ። ድመት በልቷት ይሁን ወይም አካባቢውን ለቃ ባልታወቀ ምክንያት የወፏ ከጎርጎሪዮሳዊው 2022 ጀምሮ አለመታየት በደስታ የማስፋፋት ሥራውን ለመጀመር አላጣደፈም። ይልቁንም የለመደችው አካባቢ ነውና ተመልሳ ብትመጣ ጎጆዋ ከፈረሰ የት ትገባለች የሚል ክርክር አስነሳ።

የከተማዋ ከንቲባ ወፏ አሁን እኛ ሳናባርራት ቦታውን ስለለቀች ሥራው መቀጠል ይችላል ቢሉም የጀርመን የተፈጥሮ ጥበቃ ሕግ ባለሙያዎች ግን አንቀጽ እየጠቀሱ ሞገቱ። የአእዋፍ ጥናት ባለሙያዎችም በዚህ እየተሳተፉ ነው።

ይህች ወፍ ፈጣሪ አድሏት ጀርመን ሀገር በመኖሯ ጎጆዋ ሳይፈርስ የዩኒቨርሲቲ ክሊኒኩን የማስፋፊያ ፕሮጀክት አጓተተ። ግንባታውን ለማድረግ በአካባቢው ከሚገኘው ደን የተወሰነው ይወገዳል መባሉም ሌላ ሙግት አስነስቷል።

Comments

Popular posts from this blog

Biology 200 Multiple Questions for Grade 12 Students

Prepared by: Yeshaneh Adimasu (Lecturer at Adama Science and Technology Uuniversity)                                                "Together We Can"  There are #200 multiple questions which is very helpful for all grades, especially for Grade 12 students around every corner of Ethiopia. Th questions are prepared based on the New curriculum from Grade 11 (unit 1-3) and 12 (unit 1&2) and  old curriculum from Grade 9 (Unit 1-3) and 10 (Unit 1)   Those who have interest to access the video lectures from Grade 9, 10, 11, and 12, please visit my YouTube channel "Yeshaneh Tube" on the link: https://www.youtube.com/@yeshanehtube  Further more; If you have any comment and suggestion please write on the comment section  @yeshanehtube  DO carefully !! Good luck  Instruction: Choose the correct answer from the given alternatives 1. ...

Grade 12 Biology Multiple question with answer

Prepared by: Yeshaneh Adimasu  Yeshaneh Tube Instruction: Choose the correct answer from the given alternatives  1. ________ is a mission-oriented science that focus on the protection and restoration of biodiversity and the diversity of life on the earth.   A/ Environmental Biology                    C/ Conservation Biology B/ Developmental biology                    D/ Systematic Biology   Answewr: C 2. Which one of the following is not the importance of protecting natural resources? A/ Protect wildlife and preserve it for future generations B/ Improve water quality and air quality C/ Preserve open and green spaces D/ Increase exploitation of natural resources by humans Answewr: D  3 . ________ is a strategy of increasing the micronutrients level in food group through...

Grade 12 Biology Unit 2 (#part_1): Microorganisms @yeshanehtube