Skip to main content

Posts

Showing posts from September 15, 2024

5.4 % ተማሪዎች 50% ና በላይ አስመዝግበዋል

 በ2016 ዓ.ም  5.4 በመቶ ተማሪዎች 50 በመቶና በላይ አስመዝግበዋል  ሚኒስትሩ እንደገለጹት ለአገር አቀፍ ፈተና ከተቀመጡ 674,823 ተማሪዎች ውስጥ 36, 409 ወይም 5.4 በመቶ የማለፊያው ውጤት ማግኘታቸውን ገልጸዋል። የማለፊያ ውጤት ያስመዘገቡ ተማሪዎች ቁጥር ከባለፈው ዓመት ተመሳሳይ ጊዜ በ9,114 ተማሪዎች ብልጫ እንዳለውም ተናግረዋል።  በዚህም በተፈጥሮ ሳይንስ 28,158 ወይም 9 በመቶ በማህበራዊ ሳይንስ 8,251 ወይም 2 በመቶ የማለፊያ ውጤት ማምጣታቸውን አመላክተዋል። በፈተናው 1,221 ተማሪዎች ከፍተኛ ውጤት ማስመዝገባቸውን የገለጹ ሲሆን በባለፈው  ዓመት ከተመዘገበው 220  አንጻር የተሻለ ውጤት መሆኑም ተገልጿል።  ቀደም ሲል በነበረው የመሰናዶ ትምህርት በትግራይ ክልል ፈተናቸውን ከወሰዱ ተፈታኞች መካከል ከ700 በተፈጥሮ ሳይንስ ከትግራይ ቀላሚኖ ት/ቤት አንድ ተማሪ 675 ማስመዝገቡን ገልጸዋል። በተመሳሳይ በዚህ ዓመት ፈተናቸውን ከወሰዱ ተማሪዎች መካከል ከ600 በተፈጥሮ ሳይንስ ከአዲስ አበባ አግዚሊየም ካቴድራል ት/ቤት 575 (በሴት ተማሪ) በማህበራዊ ሳይንስ ከአዲስ አበባ ኢትዮ ፓረንትስ 538 (በሴት ተማሪ) ከፍተኛ ውጤት መመዝገቡን ተናግረዋል ። በዚህ ዓመት ሁሉም ክልሎችና ከተማ መስተዳድሮች ከአምናው በተሻለ ተማሪዎችን ማሳለፋቸውን የገለጹት ሚኒስትሩ 1,363 ት/ቤቶች ግን ምንም ተማሪ አለማሳለፋቸውን ጠቁመዋል።  ሚኒስትሩ በመጨረሻም 50 በመቶና በላይ ያመጡት በቀጥታ ወደ ዩኒቨርሲቲ እንደሚገቡ ጠቅሰው የተወሰኑ ተማሪዎችም በሪሜዲያል ፕሮግራም ተጠቃሚ እንደሚሆኑ ተናግረዋል።

Happy New Year 2017 E.C

 

የትግርኛ ቋንቋና የፍልስፍና ትምህርቶች ተዘጉ !!

  የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ከ18 ዓመት በፊት የተቋቋመውን የትግርኛ ቋንቋ እና ስነ ጹሁፍ ትምህርት ክፍልን፤ በዘንድሮው የትምህርት ዘመን ሊዘጋ ነው። በፍልስፍና ትምህርት ክፍል በመጀመሪያ ዲግሪ የሚሰጠው ትምህርትም፤ ከዚህ ዓመት ጀምሮ እንዲቋረጥ ዩኒቨርስቲው ውሳኔ አስተላልፏል። አንጋፋው ዩኒቨርሲቲ ከእዚህ ውሳኔ ላይ የደረሰው፤ የትምህርት ክፍሎቹ ላለፉት አምስት ተከታታይ ዓመታት አዲስ ተማሪዎችን ባለመቀበላቸው ነው።  “ትግርኛ ለምን ተማሪ እንዳጣ ዋናው ምክንያት የታወቀ ነው። በጦርነቱ ምክንያት ነው። እሱ ጎድቶናል። ተማሪው በየት አድርጎ ይምጣ” ሲሉ የትምህርት ክፍሉ ኃላፊ አቶ ሀድጉ ተካ የችግሩን ምክንያት አስረድተዋል። የትግርኛ ቋንቋ፣ ስነ ጹሁፍ እና ፎክሎር ትምህርት ክፍል አዲስ ተማሪዎችን ለመጨረሻ ጊዜ የተቀበለው በ2010 ዓ.ም ነበር። እንደ ትግርኛ እና ቋንቋ ስነ ጽሁፍ ሁሉ በተመሳሳይ ምክንያት እንዲቋረጥ በዩኒቨርሲቲው ውሳኔ የተላለፈበት ሌላው የትምህርት አይነት፤ በመጀመሪያ ዲግሪ ደረጃ የሚሰጠው የፍልስፍና ትምህርት ነው። የፍልስፍና ትምህርት ክፍል ከ2011 ዓ.ም ወዲህ በመጀመሪያ ዲግሪ መርሀ ግብር አዲስ ተማሪዎችን አለመቀበሉን የትምህርት ክፍሉ ኃላፊው ዶ/ር ፋሲል መራዊ ለ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” ተናግረዋል።