ክፉ መሆን ክፋት ነው ።ደግ መሆን ግን ደግነት አይደለም ። ሰውነት ነው ። የተፈጠርነው ከደግ አምላክ እስከሆነ ድረስ ደግ ልንሆን ነው ። ብዙዎቻችን በክፋት ቦታ ላይ ስለታየን ደጎች ሲገኙ ፃድቅ ይሆኑብናል ። ግን ደግነት ተፈጥሯችን ነው ። ደግ ልንሆን ፣ ለሌሎች ልንሆን ነው የተፈጠርነው ። ክፋትን እንድናደርግ አልመጣንም ። አንዳችን ለሌላችን ተባባሪ ፣ ደጋፊ ስንሆን እንደተፈጥሯችን መሆን እንጂ የተለየ ሰውነት አይደለም ። ሌሎችን የምናግዘው፣ የምንተባበረው ፣ የምንረዳው ደግሞ ወደንና ደግ ሆነን ሳይሆን እኛም ያለሌሎች እገዛ ሰው መሆን ስለማንችል ነው ። ሰው የሆነው ራሱ በሰው ነው ። ሁሉ ነገራችን ፣ ተፈጥሯችን ፣ ደምና አጥንታችን ራሱ ከሌሎች የተውጣጣ ነው ። እዚህ የደረስነው በሌሎች እገዛ ነው ። ለሌሎች የምንሆነው ሌሎች ስለሆኑልን ነው ። ሌሎችን የምናኖረው በሌሎች ስለኖርን ነው ። እኛ የራሳችን ሳንሆን የሌሎች መዋጮ ነን ። ክፋት ስናደርግ " ክፉ " የምንባለው ተፈጥሯችን የክፋት ስላልሆነ ነው ። ከተፈጠርንበት ዓላማ ስለወጣን ነው ። ትዕዛዝ ስለተላለፍን ነው ። መልካምነት ግን የተፈጠርንበትን ዓላማ ማስፈፀም ነው ። በቃ ሌላ አይመስለኝም ። ከሰውነት አለመጉደል ነው።
Welcome to Yeshaneh Tube. Join our website and gate right information at the right time Yeshaneh Tube Path of wisdom