በደቡብ አፍሪካ አንዳንድ የገጠር መንደሮች አንድ የሚገርም ባህል አላቸው። አንድ ሰው ስህተት ሲሰራ በዛ መንደር ቅጣት የለም። ሞራል የሚነካ ስድብ፣ ቅስም የሚሰብር ንግግር፣ ማግለልና መድሎ፣ ከጀርባ ሆኖ በሃሜት የሰው ስጋ መብላት ሚባል ነገር የለም። ስህተት የሚሰራ ሰው ግን በአንፃሩ በገጠሩ ሰው ይከበብና ለሁለት ቀናት ያክል ከዚህ በፊት የሰራቸው መልካም ነገሮች በሙሉ ይነገረዋል። በእነሱ እምነት ሁሉም ሰው መልካም ነው። አንዳንዴ ግን ስህተት ይሰራል። ስህተት ሲሰራ፤ መልካሙን ማንነቱን ብናስታውሰው ከእውነተኛ ማንነቱ ጋር ይገናኛል ይላሉ። ይህም ተግባር #ኡቡንቱ(#Ubuntu) ተብሎ ይጠራል።

Comments
Post a Comment