Skip to main content

5.4 % ተማሪዎች 50% ና በላይ አስመዝግበዋል

 በ2016 ዓ.ም  5.4 በመቶ ተማሪዎች 50 በመቶና በላይ አስመዝግበዋል 

ሚኒስትሩ እንደገለጹት ለአገር አቀፍ ፈተና ከተቀመጡ 674,823 ተማሪዎች ውስጥ 36, 409 ወይም 5.4 በመቶ የማለፊያው ውጤት ማግኘታቸውን ገልጸዋል። የማለፊያ ውጤት ያስመዘገቡ ተማሪዎች ቁጥር ከባለፈው ዓመት ተመሳሳይ ጊዜ በ9,114 ተማሪዎች ብልጫ እንዳለውም ተናግረዋል። 


በዚህም በተፈጥሮ ሳይንስ 28,158 ወይም 9 በመቶ በማህበራዊ ሳይንስ 8,251 ወይም 2 በመቶ የማለፊያ ውጤት ማምጣታቸውን አመላክተዋል።


በፈተናው 1,221 ተማሪዎች ከፍተኛ ውጤት ማስመዝገባቸውን የገለጹ ሲሆን በባለፈው  ዓመት ከተመዘገበው 220  አንጻር የተሻለ ውጤት መሆኑም ተገልጿል።  ቀደም ሲል በነበረው የመሰናዶ ትምህርት በትግራይ ክልል ፈተናቸውን ከወሰዱ ተፈታኞች መካከል ከ700 በተፈጥሮ ሳይንስ ከትግራይ ቀላሚኖ ት/ቤት አንድ ተማሪ 675 ማስመዝገቡን ገልጸዋል።


በተመሳሳይ በዚህ ዓመት ፈተናቸውን ከወሰዱ ተማሪዎች መካከል ከ600 በተፈጥሮ ሳይንስ ከአዲስ አበባ አግዚሊየም ካቴድራል ት/ቤት 575 (በሴት ተማሪ) በማህበራዊ ሳይንስ ከአዲስ አበባ ኢትዮ ፓረንትስ 538 (በሴት ተማሪ) ከፍተኛ ውጤት መመዝገቡን ተናግረዋል ።


በዚህ ዓመት ሁሉም ክልሎችና ከተማ መስተዳድሮች ከአምናው በተሻለ ተማሪዎችን ማሳለፋቸውን የገለጹት ሚኒስትሩ 1,363 ት/ቤቶች ግን ምንም ተማሪ አለማሳለፋቸውን ጠቁመዋል። 


ሚኒስትሩ በመጨረሻም 50 በመቶና በላይ ያመጡት በቀጥታ ወደ ዩኒቨርሲቲ እንደሚገቡ ጠቅሰው የተወሰኑ ተማሪዎችም በሪሜዲያል ፕሮግራም ተጠቃሚ እንደሚሆኑ ተናግረዋል።

Comments

Popular posts from this blog

Biology 200 Multiple Questions for Grade 12 Students

Prepared by: Yeshaneh Adimasu (Lecturer at Adama Science and Technology Uuniversity)                                                "Together We Can"  There are #200 multiple questions which is very helpful for all grades, especially for Grade 12 students around every corner of Ethiopia. Th questions are prepared based on the New curriculum from Grade 11 (unit 1-3) and 12 (unit 1&2) and  old curriculum from Grade 9 (Unit 1-3) and 10 (Unit 1)   Those who have interest to access the video lectures from Grade 9, 10, 11, and 12, please visit my YouTube channel "Yeshaneh Tube" on the link: https://www.youtube.com/@yeshanehtube  Further more; If you have any comment and suggestion please write on the comment section  @yeshanehtube  DO carefully !! Good luck  Instruction: Choose the correct answer from the given alternatives 1. ...

Grade 12 Biology Multiple question with answer

Prepared by: Yeshaneh Adimasu  Yeshaneh Tube Instruction: Choose the correct answer from the given alternatives  1. ________ is a mission-oriented science that focus on the protection and restoration of biodiversity and the diversity of life on the earth.   A/ Environmental Biology                    C/ Conservation Biology B/ Developmental biology                    D/ Systematic Biology   Answewr: C 2. Which one of the following is not the importance of protecting natural resources? A/ Protect wildlife and preserve it for future generations B/ Improve water quality and air quality C/ Preserve open and green spaces D/ Increase exploitation of natural resources by humans Answewr: D  3 . ________ is a strategy of increasing the micronutrients level in food group through...

Grade 12 Biology Unit 2 (#part_1): Microorganisms @yeshanehtube