#በጉዞ_ላይ
• በተሳፋሪዎች የተሞላዉ አዉቶብስ ጉዞ ላይ ነዉ። ወዲያዉ የአካባቢዉ የአየር ሁኔታ ተቀያየረና አስፈሪ የነጎድጓድና የመብረቅ ብልጭታ መታየት ጀመረ፡፡ ተሳፋሪዎቹ አዉቶብሱ ከአሁን አሁን በመብረቅ ተመታ እያሉ መጨነቅ ጀመሩ መብረቁ ግን መኪናዉን እያለፈ ይወድቅ ነበር፡፡
• እንዲህ አይነቱ አጋጣሚ ሁለት ሶስት ጊዜ እንደቀጠለ ሾፌሩ አዉቶብሱን ከአንድ ዛፍ 50 ጫማ ርቀት ሲቀረዉ አቆመና ተሳፋሪወቹን "ከእናንተ መሃል ዛሬ መሞቱ ግዴታ የሆነ ሰዉ ሥላለ ከአሁን በኋላ አብሮን ከተጓዘ በእሱ ምክንያት ሌሎቻችንም አብረን እንዳንጠፋ ሁላችሁም በየተራ እየወጣችሁ ያንን ዛፍ እየነካችሁ እንድትመለሱ እፈልጋለሁ! መሞት ያለበት ሰዉ ካለም ዛፉን የነካ ጊዜ በመብረቅ ይመታል! ሌሎቻችን ግን እንተርፍለን ማለት ነዉ!!" አለ። ሾፌሩ ይህን ያደረገውም በተለምዶ መብረቅ ዛፍ ላይ ያርፋል ከሚባለው ብሂል ተነሥቶ ነበር።
• ሁሉም የመጀመሪያዉን ተሳፋሪ ሄዶ ዛፍን እንዲነካ መጎትጎት ጀመሩ። እሱም እየጨነቀዉና በፍርሃት ተዉጦ ሄዶ ዛፍን ነክቶ በሰላም ተመለሰ። ምንም ሳይሆን በመመለሱም ልቡ በደስታ ጮቤ ረገጠች፡፡
• መጨረሻ ላይ የነበረዉ ተሣፋሪ ተራ እንደደረሰ ሁሉም ሟቹ እሱ እንደሆነ በማሰብ ዐይኑን እያዩት እንዲሄድ ገፋፉት፤ እሱም በመሞት ፍራቻ ተዉጦ ከአዉቶብሱ ወረደ። ከዛፉ ደርሶ እንደነካዉም ኃይለኛ ድምፅ ተሠማ፤ አስፈሪ የመብረቅ ብልጭታም ሆነ።
• መብረቁ ግን የመታዉ አዉቶብሱን ነበር። በውስጡ የነበሩት ተሳፋሪዎችም ሞቱ፡፡ እነዚያ ቀደም ብሎ አዉቶብሱን ያለፉት አደጋዎች ሁሉ ያለፉትም በመጨረሻዉ ተሣፋሪ ንጽህና ምክንያት ነበር፡፡
ሁልጊዜ እራሳችንን እንደ ንጹህ አንይ።
Yeshaneh Tube
Path of wisdom
Comments
Post a Comment