......እናትነት
በአምፖል የፈጠራ ውጤቱ የምናውቀው ቶማስ አልቫ ኤድሰን
አንድ ቀን ከትምህርት ቤቱ ወደ ቤት የተመለሰው መምህሩ የሰጠውን ወረቀት ይዞ ነበር፡፡ እናም ኤድሰን ለእናቱ እንዲህ አላት “መምህሬ ይሄን ወረቀት ለእናትህ ብቻ ስጣት ብሎ ሰጠኝ” በማለት ወረቀቱን አቀበላት፡፡ እናት እንባ በአይኖቿ ሞልቶ በወረቀቱ ላይ የሰፈረውን ሀሳብ ለልጇ አነበበችለት፡፡
ያነበበችለት ሀሳብም ይህ ነበር “ልጅሽ በአስተሳሰቡ ምጡቅ (ጀኒየስ) ነው፡፡ ይሄ ትምህርት ቤት ለእሱ አይመጥነውም። ለእሱ ብቁ የሆኑ መምህራኖችም ትምህርት ቤቱ የሌለው በመሆኑ እባክሽ አንቸው አስተምሪው ይላል” በማለት እንባዋን እየጠራረገች ወረቀቱን አጣጥፋ መሳቢያ ውስጥ ከተተችው፡፡
እናቱ ካረፈች ከብዙ ዓመታት በኋላ ኤድሰን በክፈለ ዘመኑ ካሉ
የፈጠራ ውጤት ባለቤቶች አንዱና ቀዳሚው ከሆነ በኋላ አንድ ቀን እናቱ እቃዎቿን የምታስቀምጥበትን መሳቢያ ማገላበጥ ጀመረ፡፡
ባጋጣሚ የተጣጠፈች ወረቀት ከመሳቢያው ጠርዝ አካባቢ
ተሰክታ ይመለከትና አንስቶ ከፈታት፡፡
ወረቀቱ ልጅ እያለ ከመምህሩ ለእናቱ ብቻ እንዲሰጥ ታዞ የተሰጠው ወረቀት እንደነበር አውቋል፡፡ ከፍቶ ሲያነበውም ወረቀቱ ላይ የሰፈረው ሀሳብ እንዲህ ይላል “ልጅሽ የአእምሮ ችግር ያለበትና ዘገምተኛ ነው፡፡ ከዚህ በኋላም ወደ ትምህርት ቤቱ እንዲመጣ አንፈቅድለትም” ይላል፡፡
ኤድሰን ለሰዓታት ካለቀሰ በኋላ ድያሪውን ከፍቶ እዲህ ሲል ጻፈ
“ቶማስ አልቫ ኤድሰን አእምሮው ዘገምተኛ የተባለ ልጅ ነበር፡፡ ነገር ግን በጀግናዋና በልዩዋ እናቴ የምእተ ዓመቱ ጂኔስ ሁኛለሁ፡፡ ክብር #ለእናቶች
Comments
Post a Comment