Skip to main content

ሉሲ ከዛፍ ላይ ወድቃ መሞቷ በጥናት ተረጋገጠ



 በሉሲ ወይንም ድንቅነሽ ቅሪተ አካል ላይ ላለፉት 8 ዓመታት የተደረገ ጥናት ከዛፍ ላይ ወድቃ መሞቷን አረጋገጠ፡፡

የአሁኑ ጥናት እስካሁን ላልተመለሱ ሁለት ጥያቄዎች ምላሽ የሰጠ ነው ተብሏል፡፡
ጥናቱ ሉሲ ከትልቅ ዛፍ ላይ ወድቃ መሞቷና በአጭር ጊዜ በአካባቢው በነበረ ረግረጋማ ቦታ መቀበሯን እንዲሁም አልፎ አልፎ በዛፍ ላይ ወጥታ ትኖር እንደነበር ያረጋገጠ ነው፡፡
ምርምሩን ያደረጉት የአዲስ አበባ እና ቴክሳስ ሂውስተን ዩንቨርሲቲ ምሁራን ናቸው፡፡
የምርምር ቡድኑ መሪ ዶ/ር ሙሉጌታ ፍሰሃ እንደተናገሩት በተደረገው የሲቲ ስካን ምርመራ የድንቅነሽ አጥንት አሰባበር ከትልቅ ዛፍ ላይ ወድቃ መሞቷን አረጋግጧል፡፡
የአጥንቶቿ 40 በመቶ በአንድ ላይ መገኘት ሚስጥር ደግሞ ከዛፍ ላይ ስትወድቅ በፍጥነት በረግረግ መሬት ውስጥ መቀበሯ መሆኑን አስረድተዋል፡፡
ጥናቱ በዘርፉ ባለሙያዎች ዘንድ ላለፉት 42 ዓመታት የነበሩትን ጥያቄዎች የመለሰ ነው ብለዋል፡፡
የቅርስ ጥናትና ጥበቃ ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር አቶ ዮናስ ደስታ መንግስት የኢትዮጵያን የሰው ዘር መገኛነት የሚያጠናክሩ ምርምሮችን ትኩረት ሰጥቶ እንደሚደግፍ ገልጸዋል፡፡
በተለይ በእነዚህ ጥልቅ ምርምሮች የኢትዮጵያዊያን ተመራማሪዎች ተሳትፎ ተጠናክሮ እንዲቀጥል እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል፡፡
ሉሲ ወይንም ድንቅነሽ 3 ነጥብ 18 ሚሊዮን ዓመት ዕድሜ ያላትና ለሰው ዘር ምርምር መሠረት የጣለች ነች፡፡

Comments

Popular posts from this blog

Biology 200 Multiple Questions for Grade 12 Students

Prepared by: Yeshaneh Adimasu (Lecturer at Adama Science and Technology Uuniversity)                                                "Together We Can"  There are #200 multiple questions which is very helpful for all grades, especially for Grade 12 students around every corner of Ethiopia. Th questions are prepared based on the New curriculum from Grade 11 (unit 1-3) and 12 (unit 1&2) and  old curriculum from Grade 9 (Unit 1-3) and 10 (Unit 1)   Those who have interest to access the video lectures from Grade 9, 10, 11, and 12, please visit my YouTube channel "Yeshaneh Tube" on the link: https://www.youtube.com/@yeshanehtube  Further more; If you have any comment and suggestion please write on the comment section  @yeshanehtube  DO carefully !! Good luck  Instruction: Choose the correct answer from the given alternatives 1. ...

Grade 12 Biology Multiple question with answer

Prepared by: Yeshaneh Adimasu  Yeshaneh Tube Instruction: Choose the correct answer from the given alternatives  1. ________ is a mission-oriented science that focus on the protection and restoration of biodiversity and the diversity of life on the earth.   A/ Environmental Biology                    C/ Conservation Biology B/ Developmental biology                    D/ Systematic Biology   Answewr: C 2. Which one of the following is not the importance of protecting natural resources? A/ Protect wildlife and preserve it for future generations B/ Improve water quality and air quality C/ Preserve open and green spaces D/ Increase exploitation of natural resources by humans Answewr: D  3 . ________ is a strategy of increasing the micronutrients level in food group through...

Grade 12 Biology Unit 2 (#part_1): Microorganisms @yeshanehtube