ኩላሊት (የምክር ዙፋን) እና ልብ (የጥበብ ዙፋን) ከአእምሮቻን (የእውቀት ዙፋን) በተጨማሪ ማሰብ ይችላሉ ወይም Center of intelligence በመባል ይታወቃል። አእምሮ ብቻውን ምንም መስራት አይችልም ሁለቱ ማንጠሪያዎች ናቸው የራሳቸው የሆነ የእውቀት ማንጠርና በራሳቸው ማሰብ የሚችሉ ናቸው። የሃገራችን እውቀት ብዙ ዘመናትን አስቆጥሯል (ኩላሊት የሚያጤሰው ልብ የሚያመላልሰው ናላ/አእምሮ የሚያወርሰው ይባላል) በነጮጭ ግን ልብ እንደሚያስብ የተደረሰው በ1991 G.C ነው። ልብ 40000 የተለያዩ ኒውሮን (sensory neuron) ሴል (little brain in the heart) አሉት ኩላሊትና አንጀት አካባቢ ደግሞ 500 ሚሊዮን ነውሮን አሉት (sensory neuron) ። እነዚህ ሴሎች ልክ እንደ አንጎላችን ማሰብ ይችላሉ የራሳቸውንም ውሳኔ መስጠት ይችላሉ። ሰለዚህ ልብ የራሱ ሚሞሪ አለው። ግርክ ብራደን ሁለት ምሳሌዎችን አቅርቧል፡
ምሳሌ 1:- አንዲት ሴት ነበርች እናም ልቧ በጣም ስለተጎዳ ሌላ በሞተር ሳይክል አዳጋ የተጎዳ የ አንድ ወንድ ሰው ልብ በቀዶ ጥገና ተቀየረላት። ካገገመች በኋላ ምን ምግብ ይምጣልሽ ብሎ ሆስፒታሉ የሚሰጠውን ምግብ ሲያቀርብላት አልበላም አለች። ምን ነው የምትፈልጊው ተብላ ስትጠየቅ KFC (በነጮች የታወቅ ብራንድ ምግብ ነው)። ይች ሴት ግን ይህንን ምግብ በሂወቷ በልታ አታቅም ይልቁንም በጭራሽ ይህንን ምግብ እንደማትወድ ታሪኳ ያስረዳ ነበር። በኋላ ይህ ጸባይ ለምን ተቀየረ ብላ ስታስብ ልብ የተቀየረላትን ልጅ ቤተሰቦች ማፈላለግ ጀመረ ከዛም የልጁን ታሪክ ቤተሰቦቹ እንዲነግራት ስትጠይቃቸው ልጁ በጣም ይወደው የነበረ ምግብ KFC ሆኖ አገኘችው። ስለዚህ የልጁ ሚሞሪ እሷ ጋር ቀርቷል ማለት ነው።
ምሳሌ 2. ሚድ ዊየስት (Mid-west) አነስተኛ ከተማ የተፈጠረ ክስተት ነው። የ 8 ዓመት ታዳጊ ህጻን ነች ልቧ ይጎዳል ስለሆነም የሌላ የ 10 ዓመት ሴት ህጻን ልብ ተገኝቶ ይቀየርላታል። ሁሉም ተጠናቆ ቤቷ ሂዳ ማታ አስፈሪ ህልም አየች። በጣም ያቃዣታል ስለሆነም ይህ ነገር በተደጋጋሚ ስለተከሰተባትና ቅዠቱ አላቆም ሲል ሃኪሟ ጋር ትሄዳለች። ከዛም እየቃዠሁ መተኛት አልቻልኩም ብላ ትጠይቃለች? ሃኪሙም እኔ ስራየን በአግባቡ ሰርቻለሁ ለመህኑ ምንድን ነው የሚያቃዥሽን ነገሪኝ ይላታል። ልጅቷም ጫካ ውስጥ አንድ በጣም ግዙፍ ሰው ያባርራታል እሷም ትሮጣለች፣ትሮጣለች ከዛም መሬት ላይ ትወድቃለች። መጨረሻ ላይ ይደርስባታል አካላዊ ጥቃት ያደርስባታል ከዛ በኋላ ፊት ለፊቷ ቁሞ የሆነ ቃላት ይነግራትና ይገላታል። ሁሌ ህልሙ ይህ ነው። ዶክተሩ ይህ ነገር ቀላል እንዳልሆነ ብሎም ይህ ነገር ቅዠት ሳይሆን ትውስታ እንደሆነ ይገባውና የስነ_ልቦናና የፎርንሲክ ምርመራ ክፍል ይልካታል። እነሱም ነገሩን ማጼንና በምናብ መመርመር ጀመሩ ቁመቱ፣ ግዝፈቱን፣ መልኩን በምናብ መሳል ጀመሩ። በኋላ ከዚህ ሰው ጋር የተገናኘ የወንጀል ምርመራ በማድረግ ተጠርጣሪ ይይዛሉ። ከዛም አጥብቀው ስመረምሩት የ 10 ዓመት ታዳጊዋን የገደለው ወንጀለኛ እንደሆነ ተደረሰበት። ስለዚህ የ 10 ዓመቷ ልጅ ትውስታ ልብ ለተቀየረላት ልጅ ዉስጥ እንዳለ ተረዱ። ስለዚህ ልብ እራሱን ችሎ ማሰብ ይችላል።
What do you say?
ReplyDeleteእርስዎስ ምን ይላሉ?