ከንቲባ ገብሩ ተብለው ከመጠራታቸው በፊት ጎባው ደስታ በመባል ይታወቁ ነበር። ከንቲባ ገብሩ የጎንደር ከንቲባ ነበሩ። አንድ ቀን እንዲህ ብለው ነበር ኢየሩሳሌም ሄድኩና ትምህርት ቤት እንደገባሁ ሰሞን ከተማሪዎች ጋር የደረቀ ፍግ በአካፋ እየዛቅን በሚገፋ ጋሪ ወደ የአትክልቱ እንድናደርስ ታዘዝን ተማሪዎች የለመዱት ስራ ስለነበረ እየተዝናኑና እየተጫወቱ ይሰራሉ። የክፍል አለቃችን መጣና ጎባው (የገብሩ ቅጥል ስሙ ነው) አትሰራም እንዴ? ቢለኝ እኔ ፍግ ለመዛቅ አልመጣሁም ለመማር እንጅ ብየ መለስኩለት። የክፍሉ አለቃም ይህን ሂዶ ለዋናው አስተዳደር ነገራቸው። እሳቸውም ተወው ግድ የለም #አሱ #የመጣው #ስራ #መስራት #ካለመዱ #ሃገር ስለሆነ አስኪላመድ ድረስ አትንኩት ብለው ሲናገሩ ሰማሁ። እኔም ትቂት ደቂቃዎች ከቆየሁ በኋላ ቆጨኝና የሚገፋውን ጋሪና አካፋየን ይዠ እንደ ጓደኞቸ እየተሻማሁ መስራት ጀመርኩ። ከዚያ በኋላ ስራ ሂወት መሆኑን ተማርኩና ኑሮየን ማቅናት ቻልኩ።
??? እስኪ እራሳችንን እንመልከት እኔ፣ አንች። እኛና እናንተ ስራ እንወዳለን ዝቅ ብለን እንሰራለን ወይስ ሌሎች ሲሰሩ እናሾፋለን፣ ሰበበኞች ነን፣ ወደኋላ እንጎትታለን፣ ጓደኛ መስለን እሾህ እንሆናለን? እስኪ የትኛው ባህሪ እንዳላችሁ መልሱልኝ???
በርግጥ አንተ ማነህና ማንን ትጠይቃለህ ብትሉኝ ቀና ሰው ፍለጋ ብየ እመልሳለሁ።
እውነት ነው
ReplyDelete