አንድ ቄስ እና መርጌታ በመካከላቸው አለመግባባት ይፈጠራል። በዚህም ጉዳይ ቄሱ መሪጌታውን በሰው ፊት እውቅት የሌለው እደሆነ ለማሳየት አሰቡ ነገር ግን በእውቀት እንደማይደርሱበት ተገነዘቡ። ኖም ግን አንድ ቀን ሰዎች ይሄ መሪጌታ አይችልም፣ እውቀት የለውም መሪጌታ ማለት እነ እከሌ እያለ የሌላ መሪጌታ ስም መጥራት ጀመረ በመቀጠልም ይህን ለማረጋገጥ አንድ ጥያቄ ልጠይቀው ነው ይህንን ከመለሰልኝ እኔ እቀጣለሁ አለ። ለመሪጌታው እንዲህ ሲል ጠየቀው “እንዳይ” ማለት ምን ማለት ነው? አለው። መርጌታውም “እንጅ” ብሎ መለሰ ቄሱም ቶሎ ብሎ ሰማችሁት አይደል ይሄው ምንም አያቅም አላቸው። ግን እንዳይ የግዕዝ ቃል ሲሆን በአማርኛ “እንጃ” ማለት ነው። ቄሱ የተሰበሰቡት ሰዎች ግዕዝ ስለማያቁ ነበር በነሱ ዘንድ እንደ አላዋቂ እዲቆጠር የሞከረው።




Comments
Post a Comment