አንድሪ ሩሽ ይባላል የቀድሞው የአሜሪካ ሰራዊት/ጦር አባል ነበር። 23 አመት ካገለገለበት የአሜሪካ ጦር እራሱን በጡሬታ ያገለለው የ47 ዓመት አሁን ላይ እራሱን ጦሩ በማግለል በነጩ ቤተመንግስት /white house/ በሸፍነት ይሰራል። የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ከቢል ክሊንተን (Bill Clinton)፣ ጆርጅ ቡሽ፣ ባራክ ኦባማ፣ ዶላንድ ትራምፕ እነሱና ቤተሰቦቻቸው የሚመገቡትን ምግብ የሚሰራና አሁንም እየሰራ ያለ ሼፍ ነው አንድሪ ራሽ።
በነጩ ቤተመንግስት /white house/ በሸፍነት የሸፎች አለቃም ሁኖ ሰርቷል። ከሸፍነቱ በተጨማሪ በአዕምሮ ጤና ተማጋችነቱና አነቃቂ ንግግሮቹ ይታወቃል። ይህ ሰው በሂወቱ ትልቅ ትርጉም የሚሰጠውን ምልክት በቀኝ ክንዱ ላይ በንቅሳት መልክ አስቀምጧል። የራሽ ቀኝ እጁ ላይ የሰፈረው የንቅሳት ጹሁፍ በአማርኛ “#ኢትዮጵያ” ይላል። አንድ ቀን እጅ ላይ ያለውን የአማርኛ ንቅሳት ትርጉም ሲያብራራ #የጥቁር #ህዝቦች #ኩራት የሆነችውን ሃገር ለማክበር በማሰብ ነው ብሏል። አለም ላይ ልክ እንደ ራሽ ያሉ ጥቁር ሰዎች የአሸናፊነት ምልክት የሆነውን ኢትዮጵያ የሚለውን ስም አንዳንዶቹ በጡንቻቸው ብዙወች ደግሞ በልባቸው አትመውታል።
ለኛ ለኢትዮጵያዊያን ደግሞ “በእጅ የያዙት ወርቅ ከመዳብ እኩል ነው” ከሚለው አባባል እንኳን ወርደን “በእጅ የያዙት #ወርቅ #ከመዳብም ያንሳል” በሚል ብሂል በዘር በሃይማኖት በፖለቲካ ተከፋፍለን የነጻነት ቀንዲል የሆነችዋን ታላቋን አገር መቀመቅ ከተትናት። ለዚህ ደግሞ እኔም፣ አንተም፣ አንችም፣ እናንተም ሁላችንም ነን። ለታላቅነቷ ጠጠር እንደመወርወር ለመንገዳገዷ/ለድህነቷ/ መርግ ጣልንባት።

Comments
Post a Comment